0
#FastMereja I አትሌት ገለቴ ቡርቃ ለ20 ያፈራችው ንብረት በባለቤቷ ምክንያት ማጣቷን ፋስት መረጃ ገመዳ ሾው ላይ ቀርባ ባደረገችው ቃለምልልስ ተመልክቷል።
መኖሪያ ቤት እና መንግስት በተለያየ ጊዜ የሸለማት 11 መሬቶች ውስጥ አስሩ ባለቤቷ መሸጡን እና አሁን ካለችበት ቤት ለማስወጣት በፍርድ ቤት ጉዳዩን እየጨረሰ ነው ስትል አትሌቷ ተናግራለች።
ካሏት 5 መኪናዎች 4 መኪኖችን ባለቤቷ መሸጡንም ገልጻለች።
በአሁኑ ወቅት ልምምድ አቁማ በፍርሃት ለአንድ አመት ከቤት ሳትወጣ መቀመጧን ተናግራለች።
ፍርድ ቤት ሁሉንም ነገር እኔ ላይ እየፈረደ ነው የእኔን ጉዳይ እየተመለከተ አይደለም በማለት ተናግራለች።
እኔን የሚሰማኝ ጠፍቷል አሁን የቀረው ጠቅላይ ሚንስትሩ ነው ጎዳና ከመውደቄ በፊት ህዝቡ ድምጽ ይሁነኝ ብላለች።
