#FastMereja
ከባለቤቷ ጋር የተዋወቁት እሱ የታክሲ ሾፌር ነበር በተለያዩ ቦታ ስትንቀሳቀስ ያደርሳል ይመልሳል በዚህ መሃል ተግባብተው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት በ2000 ዓ.ም ወደ ትዳር እንደገቡ ፋስት መረጃ በገመዳ ሾው ላይ ስትናገር ሰምቷክ።
ምን ተፈጠረ?
በ2009 እኔ ለውድድር ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ ነበር ውድድሩን ድል አድርጌ ስመለስ በድንገት ከቤት ወጥቶ ጠፍቶ ጠበቀኝ ትላለች ገለቴ በገመዳ ሾው ብዙ አፈላለኩት ቤተሰቡን ጠየቅኩ ፀበል ሄዶ ነው የመጣል አሉኝ ከ8 ወር በኋላ በፍርድ ቤት ክስ ወረቀት መጣ ፍርድ ቤት ቀረብኩ ክሱ የሚለው ትዳሬ ይፍረስ የሚል ነበር፣ መሆን የለበትም በኃይማኖታዊ ስርዓት የተመሰረተ ትዳር ነው በድንገት መፍረስ የለበትም ብዬ ብከራከርም እሱ ካልፈለገ መፍረስ ይችላል ተብሎ ትዳሩ በፍርድ ቤት ፈረሰ ብላለች።
ከዛ በፊት ንብረቶቹን ለእሱ ስም ውክልና ሰጥቼ ነበር ከነበሩት የመኖሪያ ቤቶች እና መሬቶች መካከል በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ቦሌ፣ ገርጂ፣ የካ ፣ ሀዋሳ፣ አዳማ፣ ሞጆ፣ ሰበታ፣ ሱሉልታ እንዲሁም 5 ተሽከርካሪዎች ነበሩኝ ብላለች።
ከትዳር በፊት የነበሩኝ ቤቶች ጭምር እንደሸጣቸው ነው የሚናገረው አንድ በመንግስት የተሸለምኩት መኖሪያ ቤት እናቱ ለገሃር ጀርባ ለኑሮ ምቹ ያልሆነ ቤት ውስጥ ትኖር ስለነበር ለምን እዚህ ቤት ውስጥ አትኖርም ብዬ እሷን እዛ አስገብተን ትኖርበት ነበር እሱን ጭምር አሁን ለእሷ እንደሸጠላት ነው የነገረኝ፣ አሁን በፍርድ ቤት ውሳኔ 10 መኖሪያ ቤቶች ለእሱ ተፈርደው አንድ ቤት እና አንድ ያሪስ መኪና ላይ እየተከራከርን ፍርድ ቤት ሁለታችንም እንድንከፋፈለን ውሳኔ ሰጥቷል እሱንም ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ ነው፣ እየዛተብኝ እያስፈራራኝ ነው ብላለች።
በላቤ ያፈራውትን ንብረት ሙሉ በሙሉ አጥቼ ጭራሽ አሁን በህይውት እንዳልኖር እየተዛተብኝ ነው ህዝብ እና መንግስ ይድረስልኝ ስትል ፋስት መረጃ በገመዳ ሾው ላይ ቀርባ በእምባ ጭምር ያቀረበችውን ተማጽኖ ተመልክቷል።

3 comments
በቃ እንደገና ትሩጥ👍
Ayzosh Galate Ale kenenisa 😔
አይዞሽ ገለቴ