banner

የበዓለ ሃምሳ ቀን ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ፕሮግራም ሰኔ 8 ይከበራል

#FastMereja I በአርሞኒየም መንፈሳዊ ተሀድሶ ቤተክርስቲያን የተዘጋጀው “ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ” በሚል ርዕስ የበዓለ ሃምሳ ቀን ፕሮግራም አስመልክቶ ዛሬ ሰኔ 5/2017 ዓም ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

የበዓለ ሃምሳ ቀን ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ፕሮግራም ከአስር ዓመታት በላይ እየተከበረ ያለ በዓል መሆኑ ተገልጿል። ይህ ፕሮግራም ወንጌላውያን አማኞች ሁሉ እርስ በእርሳቸው የሚተያዩበት የጋራ በዓል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ መንፈስ ቅዱስ የሚመሰገንበት ፕሮግራም መሆኑ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

በዓለ ሃምሳ የመንፈስ ቅዱስ የወረደበት ቀን እንደመሆን ያንን ቀን በማሰብ፣ ከስላሴ አንዱ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን የምናመሰግንበት በዓል ነው። የአርሞኒየም ቤተ ክርስቲያን በዚህ መረዳት ይህን በዓል እያከበረች ነው ተብሏል።

የአርሞንየም ተሀድሶ ቤተክርስቲያን ከአስር አመት በላይ በዓለ ሃምሳን በልዩ ሁኔታ ስታከብር የቆየች ቤተክርስቲያን እንደሆነች ተገልጿል። ከዚህ በፊት በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ፣ በኢትዮጵያ ሆቴል ፣ በስካይ ላይት ሆቴል እንዲሁም በኢሊሌ ሆቴል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል።

የፊታችን እሁድ ሰኔ 8/2017 ዓ.ም ከ9:00 ሰአት ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል የሚከበር ሲሆን ሁሉም የወንጌል አማኞች በዚህ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል።





1 comment

Esubalew Bisrat June 12, 2025 - 9:02 am

ኧረ ፈዋ ካለው ሸራተን ሁላችንም እንመጣለን ክብር ለጌታ ይሁን 😍

Reply

Leave a Comment