0
#FastMereja I ብረሽድ ባይ ቤቲ የሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም 300 ሰልጣኞችን ዛሬ ሰኔ 7/2017 ዓ.ም አስመረቀ።
ላለፉት ዓመታት በተለያዩ የውበት ሙያዎች ስልጠናዎችን በመስጠት ለበርካቶች የስራ ዕድል መፍጠር የቻለ ማሰልጠኛ ተቋም መሆኑ ተነግሯል።
የብረሽድ ባይ ቤቲ ማሰልጠኛ ተቋም መስራች ቤተልሔም እስክንድር ባደረገችው ንግግር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ነጻ የትምህርት ዕድል በመስጠት መስማት የተሳናቸውን ዜጎች በመደገፍና በህጻናት ማቆያ አገልግሎቱ ስሙ ጎልቶ ይታወቃል ብላለች።
ከምንሰጣቸው ስልጠናዎች ባለፈም ተማሪዎችን በተለያዩ የውበት ሳሎኖች በማስቀጠርና የራሳቸውን የንግድ ተቋም ለሚፈልጉ እስከ 100 ሺህ ብድር በማመቻቸት የውበት ኢንደስትሪውን ለማሳደግ እየሰራን እንገኛለን ብላለች።
ድርጅቱ ከተመሰረተ በ9 አመታት ውስጥ ከ4000 በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቋል።




