banner

በ3.5 ቢሊዮን ብር የተገነባው ቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ ተመረቀ

#FastMereja I ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀገሪቱ በአይነቱ ልዩ የሆነዉን “የቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ “ መርቀዉ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸዉን ገለጹ

በሀገራችን የላቀ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል የተባለው 25 ሚለዮን ዶላር /3.5 ቢለዬን ብር/ ወጪ የተደረገበት “የቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ “ ዛሬ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቋል።

ይህ የሜድካል ፕላዛ በኢትዮጵያ ጤና ሥርዓት ላይ በርካታ እሴቶችን የሚጨምር በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ ህክምና ተደራሽነትንና ጥራትን ከፍ በማድረግ ከሃገር ውጭ ህክምና የሚያጋጥሙ ወጪዎችን የሚቀንስ ፣በተለይም እንደ ኢትዮዽያ የመጀመሪያው የአጥንት መሳሳት መመርመሪያ እና በአፍሪካም ደረጃ የመጀመሪያ የሆነዉ የልብ፣ የአንጎል እና በሰውነት ላይ የሚከሰቱ የደም ስር ችግሮችን ያለ ኦፕሬሽን መስራት የሚያስችል AI የተገጠመለት በድምጽ መታዘዝ የሚችል በአይነታቸዉ የመጀመሪያ የሆኑ የህክምና መሳሪያዎች የተገጠሙለት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ።

የቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ መስራችና ባለቤት የሆኑትን ሚስ ጄን ሊ ይህንን ዘመኑን የዋጀ የጤና ተቋም ገንብተው ለአገልግሎት ስላበቁ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይ አመት ውስጥ ለመገንባት ባቀዱት ተጨማሪ የምዕራፍ ሁለት ስራ የከተማ አስተዳደራችን የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን ለማረጋገጥ እወዳለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።





Leave a Comment