banner

የዓለም ባንኮች ቀን በተለያዩ ሁነቶች በኢትዮጵያ ሊከበር ነው።

#FastMereja I የባንኮች ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሊከበር ነው። ዛሬ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ የባንኮች ቀን በጎዳና ላይ ሩጫ እና በኤግዚብሽን እንደሚከበር ተገልጿል።

አመቱን ሙሉ በትጋት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ሰራተኞቻቸዉን ቲሸርት ገዝተዉ የሚሳትፉበት ራሳቸዉን ከሌሎች የባንኩ ማህረሰብ ጋር የሚያስተዋዉቁበት አልፎም በሰራተኞቻቸዉ አማካኝነት ራሳቸዉን የሚያስተዋዉቁበት ፕሮግራም ነዉ ተብሏል።

ይህ አመታዊ ፕሮግራም ህዳር 21/2017 ዓ.ም የሚደረግ ይሆናል። በዚህም በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የባንኩ ማህበረሰቦች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለተኛው ህዳር 25/2017 ዓ.ም የሚደረገው ኢግዚቢሽ ሲሆን ይህም ፕሮግራም ባንኮቹ ለተሳትፎ በተዘጋጀላቸዉ ድንኳኖች አገልግሎታቸዉን ያስተዋውቃሉ በዚህ ፕሮግራም ላይ ሁሉም ባንኮች በንቃት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የባንኮች ቀን የሚከበረዉ እ.ኤ.አ አቆጣጠር ዲሴምበር 4 ቀን ሲሆን የሚከበርበትም ዋናምክንያት ለህዝቡ ፋይናስ ደህንነት ባንክ መረጃን በመስጠት ለሚጫወተዉ የላቀ ሚና እዉቅናን ለመስጥ ነዉ፡፡

የፕሮግራሙ አዘጋጅ ማርዳ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ኤቨንትስ ካምፓኒ ሲሆን ከተቋቋመ ዘጠኝ ዓመት ያስቆጠረ የተለያዩ ፊልሞችን በመስራት እንዲሁም ኤቨንቶችን በማዘጋጀት በመዝናኛዉ ኢንዱስትሪ የራሱን አሻራ በማሳረፍ ላይ ይገኛል።





10 comments

Wiz Tame July 7, 2025 - 8:24 am

#Justice for Sidaama coffee

Reply
Mella Z Gunner's July 7, 2025 - 8:24 am

ምናለበት ለሁላችንም ቦነስ 10,000 ብር ቢሰጡን

Reply
Gemechu Mekonen July 7, 2025 - 8:25 am

Idar 21/2017??? weyis idar 21/2018

Reply
Elias Fedo Haro July 7, 2025 - 8:25 am

ንግድ ባንክም ባንክ ነኝ ብለው ያከብራል?😁

Reply
Teddy Abush July 7, 2025 - 8:25 am

ታድያ እነዚህ ምን አገባቸዉ

Reply
Meha Moha July 7, 2025 - 8:26 am

እና አርትስቶቹ አጨብጫቢ ናቸው🙄

Reply
Haider Abrar July 7, 2025 - 8:27 am

የአየር ጤናዎች ቀንስ🙄

Reply
Nigus Minale July 7, 2025 - 8:27 am

የቀን ስህተቱን አርሙት!!

Reply
Ađđä Xø July 7, 2025 - 8:28 am

ወደዃላ ሄደን ነው የምናከብረው

Reply
Alehu Tewelje Lulge July 7, 2025 - 8:28 am

ህዳር 2017? Already passed

Reply

Leave a Comment