banner

አዋሽ ባንክ እና M-PESA “እርፍ በኤምፔሳ” የተሰኘ በዲጂታል ቁጠባ እና በብድር አገልግሎት ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸ

አዋሽ ባንክ እና M-PESA “እርፍ በኤምፔሳ” የተሰኘ በዲጂታል ቁጠባ እና በብድር አገልግሎት ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ውል ተፈራረሙ

#FastMereja I አዋሽ ባንክ ከM-PESA ETHIOPIA ጋር በዲጂታል ቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ዙሪያ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስታራቴጂክ ፓርትነርሺፕ ውል ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራርሟል።

የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በፊርማ ስነ ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት በዛሬው ዕለት ባንኩ ከM-PESA ETHIOPIA ጋር በተደረገው “እርፍ በኤምፒሳ” የተሰኘው ዲጂታል overdraft የብድር አገልግሎት መተግበሪያ ስምምነት መሠረት ለደንበኞች የዲጂታል ማይክሮ ብድር አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊ የቴክኖሎጂ ማሻሻያዎችን እና ትስስሮችን በማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በተሻለና በላቀ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማከል ወደ ደንበኞቹ ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጸዋል።

አክለውም አጋርነቱ የአዋሽ ባንክን የፋይናንስ ጥንካሬ እና እምነት ከኤም-ፒሳ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የሞባይል ገንዘብ አመራር ስርዓት ጋር በማገናኘት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ድጂታል ብድር ለማቅረብ እንደሚያስችል ገልጸዋል። የዚህ ዲጂታል ማይክሮ ብድር ተጠቃሚዎች በቀላሉ በእጅ ስልኮቻቸው ፈጣን አገልግሎት ወዲያውኑ እንደሚያገኙ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን አክለው ተናግረዋል።

የM-PESA ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤልሳ ሙዞሊኒ በበኩላቸው ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት ምሰሶ ከሆነው አዋሽ ባንክ ጋር በመተባበር የደንበኞቻችንን የፋይናንስ ደህንነት ለማሻሻል ያለው ዕድል ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን ይህንን ራዕይ ዕውን ለማድረግ የምንችለው እንደ አዋሽ ባንክ ካሉ ተቋማት ጋር በጠንካራ አጋርነት በመስራት ብቻ ነው ብለዋል ።

የመጀመሪያ የዲጅታል ክሬዲት ምርታችን በሆነው እርፍ በኤም-PESA፣ ደንበኞቻችን የብድርግብይትን ለማስፋፋት ብቻ ሳይሆን የደንበኞቻችንን ቁጥር ለመጨመር የሚያስችል ትልቅ ዕድል መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም በመረጃ ላይ የተመሰረተ ብድር ለመስጠት የሚያስችል እና ይህም የደንበኞችን የብድር ባህሪ የበለጠ እንድንረዳ ያግዘናል ሲሉ ተናግረዋል።

አገልግሎቱ አሁን ለሁሉም የM-PESA ደንበኞች ለ90 ቀናት የቀረበ ተደራሽ፣ ቀላል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፈጣን ዲጂታል የብድር አገልግሎት ሲሆን በተለይም እያደገ የመጣውን የአነስተኛ ቢዝነሶችን፣ የቤተሰብ ኃላፊዎችን እና መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎች የፋይናንስ ፍላጎት ለማሟላት ያለመ ነው።

ይህ “እርፍ በኤም ፔሳ” የተሰኘው ዲጀታል የብድር መተግበሪያ ለብድር ብቁ የሆኑ ደንበኞች የአየር ሰዓት ወይም ዳታ ለመግዛት፣ የአገልግሎት ሂሳቦችን ለመክፈል ወይም በንግድ ስራዎች ላይ ክፍያዎችን ለመፈጸም እና የመሳሰሉ ግብይቶችን ለማከናወን እንዲሁም በትንሽ መጠን እንዲበደሩ የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል።





Leave a Comment