0
#FastMereja I ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው 2107 በጀት ዓመት 162 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም በበጀት ዓመቱ የገቢ ምንጭን በማስፋት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡
በዓመቱ 162 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰው በዚህም የእቅዱን 99 በመቶ ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የ73 በመቶ እድገት ማሳየቱን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በዚህም ተጨማሪ 68 ነጥብ3 ቢሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት 6 ነጥብ 2 በመቶ መጨመሩን ጠቁመው የሕዝብ ሽፋኑም 99 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱን አብራርተዋል፡፡

10 comments
በዘረፋ ነዋ ምድረ ፈርሳም
Eh***ህጋዊ ሌባ ያተርፋል እንጅ ምን ጎሎት
ምን አገባን እኛን😏
አንዱ ቢሊዮን የኔ ነው 🤔
ምርጥ ህጋዊ ሌ*..እኮ ነው ያውም በጠራራ ፀሐይ
ይሄ ሌባ ድርጅት እኛ ሳፋሪ ይኑርልን
ዓ.ም ቱ🙄🙄
ሕጋዊ ሌባ
ብቻ የኢትዮጲያን ሕዝብ ያደከየው ድሃ ያደረገው ብቸኛው ተቋም ኢትዮ ቴሌኮም ብቻ ነው።
ዘረፈ አትልም ገቢ እኮ የሚባለዉ ሰርቶ ያተረፈ ነዉ😂