banner

የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አርቲስቶች እና ጋዜጠኞች በተገኙበት በጋምቤላ ተካሄደ።

#FastMereja I ግሪን ዌቭ አሊያንስ ከጋምቤላ ክልል ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ተካሄደ።

700 ሚሊዮን በአንድ ጀምበር የመትከል አንዱ አካል የሆነው መርሃ ግብሩ በጋምቤላ ክልል 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል እቅድ ተይዞ በዛሬው እለት ከማለዳ ጀምሮ ህዝቡ አሻራውን እያስቀመጠ ይገኛል።

የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ላይ አሻራቸውን ያስቀመጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢፋ ሙለታ፣ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ነፊሳ አልማሃዲ፣ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፓል ቱት፣ የግሪን ዌቭ አሊያንስ መስራች አርቲስት ሚካኤል ነጋሳ እንዲሁም የሀገራችን አንጋፋ እና ወጣት አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮች አሻራቸውን አስቀምጧል።





1 comment

ፍቅር ያሸንፋል July 31, 2025 - 11:43 am

የነዚህም ዘፈን፣ፊልም አናዳምጥም ፣አንሰማም የሚል አጀንዳ አይጠፋም😂

Reply

Leave a Comment