0
#FastMereja I “ማረሚያ ቤቶች የእውቀት ማዕከላት ናቸው” በማለት ባወዚር ትሬዲንግ ዛሬ ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም ለምስራቅ ሸዋ ማረሚያ “የስራ እድል ፈጠራ” በሚል የመክፈቻ እና የስራ ማስጀመርያ ስነስረዓት ተካሄዷል።
#FastMereja I የባውዚር ትሬዲንግ ባለቤት አቶ መሐመድ ሰዒድ ከትናንት በሸገር ከተማ ማረሚያ ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ማረሚያ ያደረጉት ድጋፍ ታራሚዎች አምራች ዜጋ ሆነው እንዲወጡ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዳደረጉ ተናግሯል።
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን እና የባወዚር ትሬዲንግ ንግድ ድርጅት መካከል በተደረገ ስምምነት ለምስራቅ ሸዋ ማረሚያ ለታራሚዎች የኢንዱስትሪ ልብስ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት፣ ገጠማ/ተከላ እና ጥገና እንዲሁም ነጻ ስልጠና ለመስጠት የታሰበ ነው።
ባወዚር ትሬዲንግ ንግድ ድርጅት በ2010 ዓም የተመሰረተ ሲሆን ኤሌክትሮኒክስ እና ማሽኖችን ኢምፖርት ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው።




