banner

“ሂድና” ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው

#FastMereja I በዘአራዳ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በቢኒ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው “ሂድና” የተሰኘው በአባይ ዙሪያ የተሰራውን ፊልም በአደዋ ሲኒማ ነሐሴ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ሊበቃ መሆኑን በዛሬው ዕለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።

የሂድና ፊልም አዘጋጅ እና የቢኒ ፊልም ፕሮዳክሽን ባለቤት አቶ ቢኒያም ሽፋ ፊልሙ ካሁን ቀደም በተለያዩ ሀገራት በማሳየት ለግድቡ ገቢ የማሰባሰብ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

የአባይ ወንዝ ኬት ይነሳል የሚለው በስፋት የሚያስቃኝ ፊልም መሆኑን በማንሳት በቀጣይ ከሲኒማ ባሻገር ሁሉም በቤቱ ሆኖ የሚመለከትበትን ሁኔታ ለመፍጠር እቅዶች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

በአባይ ወንዝ ላይ ያተኮረው ሂድና የተሰኘው ፊልም በነገው እለት በአድዋ ሙዝየም በፓንአፍሪካ አዳራሽ ከቀኑ 9 ለእይታ ይበቃል





1 comment

ፍቅር ያሸንፋል August 9, 2025 - 10:32 am

የፊል እርእስ ከፋባቹዋ ሂድና😄

Reply

Leave a Comment