0
#FastMereja I ዎላይታ ሶዶ ከተማ መሃል ቀበሌ ውስጥ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል አከባቢ ራሱን ዶክተር ነኝ በማለት ሲያጭበረብር የነበረ አንድ ግለሰብ የሞባይል ስልክ ሲሰርቅ መያዙን የቀበሌው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ብረሃኑ ባልቻ ገለፁ።
አቶ አንድነት አሻግሬ የተባለ ግለሰብ በቀን 03/11/17ዓ.ም ከአልማዝ ፔንሲዮን ቻርጅ ላይ የነበረውን የሌላ ሰው ንብረት የሆነውን 20 ሺህ ብር የሚገመት S8 SAMSUNG ሞባይል ስልክ ሰርቆ ሊያመልጥ ሲሞክር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው።
ኢንስፔክተር ብረሃኑ ባልቻ እንደገለፁት ግለሰቡ ራሱን ዶክተር ነኝ በማለት ህብረተሰቡን ሲያጭበረብር የነበረ ነው።
የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮ/ር ሀብታሙ አሰፋ በበኩላቸው ወንጀለኞች ወደ ተለያዩ የህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት መስለው ገብተው ወንጀል ሊፈጽሙ ስለሚችሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ በየዋህነት ከማለፍ ይልቅ ለፖሊስ ጥቆማ ማድረግን ህብረተሰቡ ባህል ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል ።
#ችሎት

2 comments
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንታ
አልፋ የሚባል በወጣቶች የሚነግድ በኢትዮጵያ የተከለከለውን ፒራሚድ ንግድ የሚሰራ ተቋም ቢሮ ከፍቶ እየሰራነው መንግስት አንድ ይበለው