0
#FastMereja I የጤና ልማት እና ፀረ ወባ ማህበር ከ27 አመት በፊት የጎጃም አካባቢን ትኩረት አድርጎ የጀመረውን እንቅስቃሴ በተሞክሮዎቹ በማጎልበት አድማሱን በማስፋት ሶስት ድርጅቶችን በማቀፍ በአስር ክልሎች ውስጥ በወባ ላይ ፕሮጀክቶችን እየተገበረ 27 አመት ሞልቶታል።
የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር መስራች የሆኑት እና ለ27 አመታት ማህበሩን የመሩት የክብር ዶክተር አበረ ምህረቴ በሰጡት መግለጫ ማህበሩ 27ኛ አመቱን ሲያከብር ሁለት አላማዎችን አንግቦ እንደሆነ ገልጿል አንደኛው የሀያ ሰባት አመት ጉዞው ለታሪክ እንዲቆይ ሌሎችም ድርጅቶች ታሪካቸውን ጽፈው እንዲያስቀምጡ ቀስቃሽ እንዲሆን “ፈጥኑ ደራሹ ማኀበር” የተሰኘ መጽሐፍ የተዘጋጀ ሲሆን ነሃሴ 17/2017 ዓ.ም በኔክሰስ ሆቴል ይመረቃል ያሉ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በወባ ላይ የሚደረገውን እርብርቦች ለማነሳሳት እና ህብረተሰቡ እንዳይዘናጋ ማድረግ እንደሆነ ተናግሯል።
ሁሉም ሰው በአመት 1ሺህ 200 ብር ለፀረ ወባ ማህበር በማዋጣት አባል በመሆን ተረባርበን ወባን ማጥፋት አለብን ሲሉ ጥሪ አቅርቧል።




