0
#FastMereja I ደብል ትሪ ባይ ሒልተን ሆቴል (Double Tree by Hilton) በአዲስ አበባ ስራ መጀመሩ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ቦሌ ብራስ ጋር የተከፈተው ደብል ትሪ ባይ ሒልተን 105 ዘመናዊ እና ቅንጡ የእንግዳ ማረፊያዎች ጨምሮ የተንጣለሉ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን የያዘ እንደሆነ የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አበረ አምሳሉ ተናግሯል፡፡
በአለም ላይ ከ60 በላይ ሀገሮች ሆቴል አገልግሎትን የሚሰጠው ሆቴሉ ከ700 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን በኢንዱስትሪው ከ55 በላይ አመታትን አስቆጥሮል።
ደብል ትሪ ባይ ሒልተን ሆቴል ከምቹ ማረፊያ በተጨማሪ በሬስቶራንቱ የምግብ እና የመጠጥ አማራጭ ሲኖረው የጂም እና ስፓ አገልግሎት እንዳለው ተገልጿል። ተከፍቶ ስራ ከጀመረ 3 ወር በላይ ሲሆነው በአሁኑ ወቅት ለ160 ሰዎች የስራ ዕድል ፈጥሯል።
1050 ካሬ ላይ ያረፈው ሆቴሉ ሰርቶ ለማጠናቀቀ 13 አመታትን ወስዷል።
#ቢዝነስ




