0
#FastMereja I የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዓለም አቀፍ የጥራት መለኪያ መስፈርቶችን መሠረት አድርጎ ባዘጋጀው የልህቀት ሞዴል (EQA Excellence Model) አማካኝነት በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ስር የሚገኙ 19 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለመመዘን እና በጥራት ጉዳዮች ላይ ከተቋሙ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት (MOU) ዛሬ ነሃሴ 21/2017 ዓ.ም ተፈራርሟል።
ስምምነቱ ማህበረሰቡ የመድሃኒት አቅርቦት ጋር ያለው ቅሬታ ማህበረሰቡ የመድሃኒት አጠቃላይ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያለው ቅሬታዎችን በምን መልኩ መፍታት እንዳለበት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት በአገራችን የጥራትን ጽንስ ሐሳብ ለማስረጽ እና ጥራት ያለው ምርት እና አገልግሎትን ለማበረታታት መንግሥት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ የተቋቋመ ድርጅት ነው።




