banner

ሄንከን ኢትዮጵያ ያስገነባውን የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አስመረቀ።

#FastMereja I ሄንከን ኢትዮጵያ የማህበረሰብ ኃላፊነት ለመወጣት እየሰራ የሚገኘው ፕሮጀክት አንዱ የሆነው ሰዎችን በማሰልጠን ወደ ስራ እያስገባ ሲሆን ከማህበረ ህይወት ፎር ሶሻል ዴቨሎፕመንት እና ከኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የኮየ ፈጬ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክትን ዛሬ ነሃሴ 22/2017 ዓ.ም የሄንከን ቢራ የስራ ኃላፊዎች፣ የኮዬ ፈጨ ክፍለ ከተማ መስተዳደር ኃላፊዎች እና የማህበሩ አባላት በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

ፕሮጀክቱ የዶሮ እርባታ፣ የከብት ማደለብ፣ የወተት ተዋጽኦ ሲሆን ለ45 ሰው ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።

ፕሮጀክቱ 20 ሚለዮን ብር የተሰራ ሲሆን ከቂሊንጦ ፕሮጀክት ጋር አብሮ 33 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኖበታል።

ለፕሮጀክቱ መሳካት አስተዋፆ ያደረጉ አካላት እውቅና ተሰጥቷል።





1 comment

የኛ ስፖርት /SPORT ENGLISH August 28, 2025 - 3:03 pm

ቂሊንጦ ፕሮጀክት 🤔

Reply

Leave a Comment