banner

የኢቢሲ ሎጎ የሰረቀው ግለሰብ 7 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

#FastMereja – በዎላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /EBC/ የዎላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ ሎጎ የሰረቀው ግለሰብ 7 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የአራዳ ቀበሌ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ደርጉ አሳሌ ገለፁ።

ተከሳሹ አቶ ትዕዛዙ መና በቀን 20/12/17ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ሰዓት አከባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ በግምት 50 ሺህ ብር የሚያወጣ የኢቢሲ ሎጎ ሰርቆ ሊወጣ ሲሞክር ለፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል።

ጉዳዩም ተጣርቶ በቀን 23/12/17ዓ.ም በዋለው ችሎት የሶዶ መጀመሪያ ጀረጃ ፍርድ ቤት ግለሰቡ ላይ የ7 ዓመት ጽኑ እስራት መፍረዱን የአራዳ ቀበሌ ታክቲክ ምርመራ ሃላፊ ዋ/ሳጂን እስጢፋኖስ አማኑኤል ተናግረዋል።

#ችሎት

2 comments

Alemayehu Admasu August 29, 2025 - 5:26 pm

Alamaw mn nber

Reply
Daniel Tedemet August 29, 2025 - 5:26 pm

ምን ሊያረገው

Reply

Leave a Comment