banner

ት/ቤቱ ለትርፍ ብለን የከፈትነው ሳይሆን ትውልድ ለመቅረጽ በማሰብ ነው

#FastMereja – የትውልድ ጉዳይ ያገባናል ባሉ ውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አማካኝነት የተከፈተው ሪም መዋዕለ ህፃናት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ህጻናት እኛ ጋር በሚቆዩበት ጊዜያቶች የሀገራቸው ታሪክ ባህል እና ቋንቋ ጠንቅቀው እንዲያቁ ተደርጎ የትምህርት ስርአቱ መቀረጹን ገልጸዋል።

ተማሪዎቻችን የራሳችን ልጆቻችን ናቸው ያሉት የት/ቤቱ የቦርድ ሀላፊ ት/ቤቱ ለትርፍ ብለን የከፈትነው ሳይሆን ትውልድ ለመቅረጽ በማሰብ ነው ብለዋል።

ነገ የተሻለ ትውልድ እንዲኖር ከተፈለገ ትምህርት ላይ መሰራት ግዴታችን ልናደርገው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

ሪም መዋዕለ ህጻናት በ2018 ዓ.ም ለችግረኛ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው የመማሪያ ቁሳቁስ እገዛ እና የነፃ የትምህርት እድል ማዘጋጀቱን በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በመርሀገብሩ እንደተገለጸው ት/ቤቱ ከኬጂ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን የሚቀበል ሲሆን የአካቶ ትምህርት የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎችም እንደሚቀበል ተገልጿል።

በቀጣይ አመት ለችግረኛ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው የመማሪያ ቁሳቁስ እገዛ እና የነፃ የትምህርት እድል ማዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ይህ አይነት ድጋፍ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

#ቢዝነስ





1 comment

Rational Previews August 29, 2025 - 4:10 pm

haaaaaa

Reply

Leave a Comment