#FastMereja – ጳጉሜ አብ ፌስቲቫል ኃ.የተ.የግል ማህበር ጳጉሜ “የአፍሪካዊያን ወርቃማ ወር” በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ልኡካን ቡድኖች ወደ ሀገራችን በመምጣት በፌስቲቫሉ ላይ በመገኘት ስለሀገራችን ባህል ወግ ትውፊት ለመረዳት እንዲሁም ያላቸውን ኢንቨስትመት እንደ አማራጭ በማቅረብ እርስበእርስ ያለንን ባህላዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማዳበር ትልቅ እድል የሚፈጥር ዝግጅት እንተዘጋጀ ተገልጿል።
የጳጉሜ ፌስቲቫል የጳጉሜ ወርን አለማቀፍ ይዘት ያለው ከመላው አገራችን እንዲሁም ከመላው አፍሪካ በየአመቱ የባህል ቡድኖች የሚመጡበት የ13ኛው ወርን ታዋቂ ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄደው ጳጉሜ ፊስቲቫል በየእለቱ የተለያዩ ክንውኖች የሚኖሩ ሲሆን
ጳጉሜ 1፣ ጳጉሜ ለሰላምና ለፍቅር
ጳጉሜ 2፣ ጳጉሜ ለባህልና ለአፍሪካ አንድነት (ፓን አፍሪካን ደይ)
ጳጉሜ 3፣ ጳጉሜ ለልጆች እንዲሁም ታላቁ ሩጫ በዝናብ ላይ
ጳጉሜ 4፣ እንነግድ በጳጉሜ
ጳጉሜ 5፣ የጳጉሜ ቆንጆ
ፌስቲቫሉ ከጳጉሜ 1-5 /2017 ዓ.ም በእንጦጦ ፓርክ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ይካሄዳል።
ጳጉሜ አብ ፌስቲቫል ኃ.የተ.የግል በሀገራችን ሀገር አቀፍ ፌስቲቫል በመባል ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ፓተንት ፍቃድ ኖሮት ፈስቲቫሎችን እያዘጋጀ ይገኛል።
#ኹነት




