banner

የግዕዝ ባንክ የተገዙ አክሲዮኖች ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ተዘዋወሩ።

#FastMereja – አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በግዕዝ ባንክ አ.ማ ፈራሚዎች የተገዛ አክሲዮን ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ መዛወሩን ገለጸ

በአደራጆችና ፈራሚዎች ስምምነት መሰረት የግእዝ ባንክ አ.ማ የምስረታ ሂደቱ ተቋርጦ ለአክሲዮን መግዣ ያዋሉት ገንዘብ ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ለአክሲዮን መግዣ እንዲዉልላቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ተገለጸ፡፡

ባንኩ እንዳስታወቀው በምስረታ ላይ የነበረው ግእዝ ባንክ አ.ማ በአደራጆችና ፈራሚዎች ስምምነት መሰረት የምስረታ ሂደቱ ተቋርጦ ለአክሲዮን መግዣ ያዋሉት ገንዘብ ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ለአክሲዮን መግዣ እንዲዉልላቸዉ ያቀረቡትን ጥያቄ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል ተቀባይነት አግኝቶ በመጽደቁ የግዕዝ ባንክ ፈራሚ ባለአክሲዮኖች ባንኩን መርጠዉ አብረዉ ለመስራት በመፍቀዳቸዉ የተሰማዉን ደስታ ገልጿል፡፡

#ቢዝነስ

4 comments

ሮዛ ፓርክስ August 29, 2025 - 1:28 pm

ሰላም ለኪ
አንበሳ 😎

Reply
Ena Ni August 29, 2025 - 1:30 pm

የትላንት ዜና 😭

Reply
ጤና አዳም August 29, 2025 - 1:32 pm

እንዲህ ነው በጊዜ ላሽ ማለት!

Reply
ተመስገን ማከይ August 29, 2025 - 1:32 pm

አርማቸውን የአክሱም ሀውልት ሲሆን ጠርጥሬ ነበር

Reply

Leave a Comment