banner

ኢትዮጵያ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለማስተናገድ ጥሪ አቀረበች

#FastMereja – ኢትዮጵያ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2029 ወይም 2031 ለማዘጋጀት ለዓለም አትሌቲክስ ጥሪ አቅርባለች።

ሻምፒዮናውን ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው ሃገራት በቶኪዮ በተዘጋጀው የኦብዘርቨር መርሃግብር ላይ ከመንግስትና ከፌዴሬሽኑ የተወጣጡ አመራሮች የተካፈሉ ሲሆን ልምድና ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበተል።

በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ እየተሳተፉ ያሉት የፌዴሬሽኑ አመራሮች በቶኪዮ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም በመዘዋወር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ልምድ ልውውጥና ተሞክሮ አድርገዋል።

#ስፖርት

Leave a Comment