banner

ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደን እና ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መረጠ።

📌የታማኝነት መገለጫ የሆነው የጋዜጠኝነት ሙያ ባለሙያዎችን የመረጥነው ድርጅቱ ታማኝ አገልጋይ በመሆኑ ነው ።

#FastMereja – ኢትዮፒካር ዘመናዊነትን የተላበሱና ለኢትዮጵያ መልካ ምድር ተስማሚ የሆኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣትና ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነትን እና ታማኝነትን ማግኘት የቻለ ድርጅት ነው።

“ታማኝነት”ን ተቀዳሚ መርሁ ያደረገው ድርጅቱ፤ በቀጥታ ግዢ ከሚያቀርባቸው መኪኖች በተጨማሪ ከተለያዩ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር (አሚጎስ ብድርና ቁጠባ፣ግሎባል ብድርና ቁጠባ )እና ከሌሎችም የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር በውስን ቁጠባ እና መጠነኛ ወለድ ብድር አማራጭን በመጠቀም እስካሁን ለበርካታ መኪና ፈላጊዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን አስረክቧል።

በአሁኑወቅት ወደ ሃገር ውስጥ በሚያስመጣቸው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖቹ ከፍተኛ ተፈላጊነትን ያገኘው ኢትዮፒካር ተወዳጆቹን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዎች በዛሬው ዕለት ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ይሰይማል።

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ብሎም በሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢነት ለረጅም አመታት በሙያው የቆዩት ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማ እና ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ የድርጅቱ አምባሳደር ተደርገው ሲሰየሙ የጋዜጠኝነት ሙያ የታማኝነትና የሃቀኝነት ሙያ መሆኑን መነሻ በማድረግ ብሎም ኢትዮፒካርም ታማኝ አገልጋይ መሆኑን ለማሳየት ነው ።

በተጨማሪም ሁለቱ ተወዳጅ ጋዜጠኞች ብራንድ አምባሳደር ሆኖ መመረጥ ድርጅቱ ለጋዜጠኝነት ሙያ እና ባለሙያ ያለውን ክብር ማሳያም ስለመሆኑ በፅኑ ያምናል።

ብራንድ አምባሳደር ሆነው የተመረጡት ዮናስ ከበደ እና እፀገነት ይልማ በአምባሳደርነት በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው በተለይም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፈላጊዎች ኢትዮፒካር የሚያስመጣቸውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ ምርጫቸው እንዲያደርጉ የማስቻል ስራን እንደሚሰሩ ይጠበቃል።

በአዲስ አበባ እና በዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ ( U.A.E) መቀመጫውን አድርጎ የተመሰረተው ኩባንያው ከኤሌክትሪክ መኪና አምራች ድርጅቶች ጋር ስምምነት በመግባት ለመኪኖቹ የባትሪ ዋስትና በመስጠት እንዲሁም የተሟላ መለዋወጫ አቅርቦትና አስተማማኝ ጥገና ጋር በማቅረብ ደንበኞቹ ከስጋት ነጻ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ አስችሏል፡፡

#ቢዝነስ




1 comment

Mìskìr Gêtú September 19, 2025 - 12:34 pm

አምባሳደር ግን ምንድነው 🤔

Reply

Leave a Comment