banner

የጉራጌ ልጃገረዶች እና የወጣት ወንዶች በዓል የሆነው አዳብና በአዲስ አበባ ሊከበር ነው።

#FastMereja I አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኀበር እና አክራሚ የሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በጥምረት አዳብና በፌስቲቫል ደረጃ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ለማክበር እንደተዘጋጁ ዛሬ መስከረም 09/2018 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳብና በአዲስ አበባ ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ቀደም ብሎ መስከረም 24/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በኬላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ተነግሯል።

የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ስነስርዓት ሲሆን 800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር ኖሯል።

አዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ይህ ድንቅ የሆነ የአዳብና ባህል በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በUNESCO እንዲመዘገብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

መላው ኢትዮጵያውያን መስከረም 24 ኬላ እና ጥቅምት 02 በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ የሚከበረውን ፌስቲቫል ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርበዋል።

#ኹነት #ማህበራዊ





1 comment

Gordena Online September 19, 2025 - 1:38 pm

የክስታኔ አዳብና በአዲሰ አበባ!
… ❤❤❤—

Reply

Leave a Comment