ሰላም ሪያሊቲ ዲኮር እና ኤቨንት ለአዲስ አመት በአዲስ ነገር መምጣቱ ተገለጸ
#FastMereja I ሰላም ሪያሊቲ ዲኮር እና ኤቨንት በዘርፉ ለየት ያሉና ለዝግጅቶች ድምቀት እና ትዝታን ለመፍጠር በአዲስ አመት አዳዲስ ስራዎች እና ፈጠራዎች መምጣቱን የድርጅቱ መስራች ወ/ሮ ሰላም ለገሰ በዛሬው እለት መስከረም 10/1/2018 አስታዉቋል።
ሰላም ሪያሊቲ እና ኤቨንት ዋነኛ አላማዉ የተለያየ ዝግጀቶችን በተሳካ ሁኔታ እንዲከወኑ ከሀሳብ ማመንጨት እስከ አፈፃፀም በመከታተል ማገዝ እንደሆነ እና ይህን ድርጅት መክፈት የልጅነት ህልሟ እንደነበር ገልፃለች።
ሰላም ሪያሊቲ እና ሌቨንት የተለያዩ ዝግጅቶች አቅድ ማዘጋጀት ዲኮር ስራ፣ የተለያዩ አበባዎችን እና የመድረክ መብራቶችን ማቅረብ እና ደንበኞች እንደፍላጎታቸዉ መድረኮችን የማሳመር እና መሰል አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል።
ድርጅቱ በሰርግ፣ በተቋማት ዝግጅቶች፣ ልደት ወይም በሌሎች ዝግጅቶች ላይ ሀሳብን ወደ እውን የመቀየር ቁርጠኛ አቋምን ይዞ የተመሰረት እንደሆነ ተገልጿል።
#ቢዝነስ




