banner

በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የአቋም መግለጫ

#FastMereja I የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ግብረ ሰ ዶማዊነት ላይ የአቋም መግለጫ አውጥታለች

በነፃነት ስም አንድ አንድ ሃገራት የግብረ ሰ ዶማዊነትን እንቅስቃሴ ህጋዊ ሽፋን ሰጥተው ትውልዱን ለማምከን ቀን ከለሌት እየተጉ ስለመሆናቸው አይኑን ለገለጠ ሁሉ የሚታየው ዘግናኝ እውነታ ነው ያለው መግለጫው ግብረ ሰ ዶማዊነት ከሃይማኖት አንጻር ብቻ ሳይሆን ከማህበራዊ ግንኙነት ረገድም እንቅፋት በመሆኑ የሚወገዝ በአገራችን ኢትዮጵያ በአማካኝ ከዘጠና በመቶ በላይ ያለው ህዝብ በተለያየ ሐይማኖት ውስጥ የታቀፈ በመሆኑ ይህን አስተሳሰብና ተግባር በየትኛውም የሃይማኖት ተቋም ተቀባይነት ያለው አይደለም ብሏል።

ከዛሬ 33 ዓመት በፊት የተመሠረተችው የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ትውልድ በእግዚአብሔር ብርሃን ይመላለስ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮትን ለሁሉ ስታደርስ ቆይታለች የተባለ ሲሆን ቤተክርስቲያኗ በአገልግሎት ከተገለጠችበት ጊዜ አንስቶ ክርስቲያኖች ከኃጢአት እና ከአመጽ ሁሉ እንዲርቁ እያስተማረች ሲሆን ዛሬም የሰው ልጆች ሁሉ እንዲያወግዙት የተገባውን የግብረ ሰ ዶማዊነትን እንቅስቃሴ በተመለከተ መግለጫ አውጥታለች።

በዚህ መሰረት ቤት ክርስትያኗ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝንና የሚያስቆጣ፣ ትውልዱን ለከፋ መንፈሳዊ ፤ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ቀውስ የሚያጋልጥ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፣ ኢ-ተፈጥሯዊ፣ ኢ-ሰብአዊና ኢ-ሞራላዊ ድርጊት ወይም ኃጢአት መሆኑን የሚያስረግጥ ትምህርተ መለኮት መኖሩን አበክረን እናምናለን ያለች ሲሆን የእምነት አባቶችም ሆኑ ሐዋርያት የዚህን ድርጊት አስከፊነት ተረድተው በመንፈስ ቅዱስ በመነዳት በዝርዝር እና በጥልቀት እንደኮነኑትና እንዳወገዙት ቅዱስ ቃሉ ገላልጦ ያስተምረናል ስትል ተደምጣለች።

በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ በአዲሱ ኪዳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ወደ ምድር በመምጣት ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ በመሞቱ ሞታችንን በሕይወት፣ ኃጢአታችንን በእርሱ ጽድቅ፣ እርግማናችንን በበረከት፣ ከእግዚአብሔር ተለይተን የነበርንበትን የቁጣ ልጅነት ወደ እግዚአብሔር የልጅነት ሥልጣን ለውጦታል ይህ የድነት ወንጌል በቤተ ክርስቲያን በኩል ለፍጥረት ሁሉ ተሰብኳል፤ ይሰበካልም ያለች ሲሆን ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በግብረ ሰ ዶማዊነት አስተሳሰብና ተግባር ውስጥ ላሉት ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር የርህራኄ ልብ ከዚህ የጥፋት አዘቅት ውስጥ እንዲወጡ ወንጌል ልትሰብክላቸው ይገባል ብላለች።

የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በደሙ የማይነጻ ኃጢአት፣ በሥሙም ሃይል የማይሰበር እርግማን፣ ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ ሃይልና በቃሉ ጉልበት የማይበጠስ እስራት የለም ያለች ሲሆን ስለዚህ ለእነዚህ ወገኖች ወንጌልን ከመስበክ ጎን ለጎን በስነ ልቦናና በህክምና ባለሙያዎች የተደራጀ የአማካሪዎች ቡድን በማዋቀር በንስሐ ለሚመለሱት የምክር አገልግሎት በመስጠት መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ልታደርግ ይገባል ያለች ሲሆን ቤተ ክርስቲያን በአገር አመራርና አስተዳደር፣ ፖሊሲን በማርቀቅ
እንዲሁም በህግ ማውጣትና ማስፈጸም ለተሰማሩ የአገር ባለ አደራዎች የትውልድ አደራ እንዳለባቸው በመገንዘብ ከመቼውም በላይ የህዝብን ስነ ልቦና ፣ ጤናና ማህበረሰባዊ ሕይወት በመጠበቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አደራዋንና የሐዋርያዊ የተልዕኮ ጥሪዋን አስተላልፋለች ፡፡




1 comment

Eto-kranyo Eto-Kranyo September 24, 2025 - 1:21 pm

አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው።

Reply

Leave a Comment