banner

በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ የ30 በመቶ ግብር በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ መደረግ ይጀምራሉ ተባለ

#FastMereja I​ የገንዘብ ሚኒስቴር ከ2018 የበጀት ዓመት ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ 30 በመቶ ግብር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማረጋገጡ ተሰማ። ይህ አዲስ ግብር 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና 15 በመቶ የኤክሳይዝ ቀረጥን የሚያካትት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይህ እርምጃ በአገሪቱ የፋይናንስ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑና የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

​ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባቀረቡት አጠቃላይ የዜጎች በጀት ዉስጥ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የግብር አይነቶችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።

​በዚህ መሰረት፣ ከነዳጅ ላይ ከሚጣለው አጠቃላይ 30% የኤክሳይዝ ታክስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ በተጨማሪ፣ የንብረት ታክስ ይገኙበታል። እንዲሁም አማራጭ አነስተኛ ታክስ እና የቅድመ ግብር ክፍያ በተመሳሳይ መልኩ በ2018 በጀት ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ካፒታል ጋዜጣ ለመረዳት ችሏል።

​ነዳጅ በማዕከላዊነት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የግብር ጭማሪው የዋጋ ግሽበቱ እንዲባባስ ያደርጋል የሚል ስጋት ሲከሰት እንደነበር ይታወሳል።

ዘገባው የካፒታል ጋዜጣ ነው
#ቢዝነስ

8 comments

Berhanu Alemayehu September 29, 2025 - 9:52 am

Congratulations

Reply
Berhanu Betha September 29, 2025 - 9:52 am

ነገርማ እየፈለጉን ነው

Reply
Ťõlinä Wørķű September 29, 2025 - 9:52 am

ቻል እንግዲህ

Reply
Amena B Chasa September 29, 2025 - 9:53 am

Thank you…enamesegnalen. ywetal yetebalew nedaj gn endet hone?

Reply
የማዳም ተሽከርካሪ የሪያል አፍቃሪ September 29, 2025 - 9:53 am

ይበለው
ፋኖን አልያም ኦነግን ተቀላቅሎ ማይታገል ከሆነ ለምን 300000000% አያስከፍለውም
ከዚህ ቡሃላ የምናዝንለት ህዝብ የለም
ታግሎ ይሄን አውሬ አገዛዝ ማስወገድ በእጁ ነው ያለው❗❗

Reply
Mignote Milky September 29, 2025 - 9:53 am

ነዳጅ በመስከረም ለገበያ ይቀርባል ተብሎ የለ ታዲዪ የምን ቫት ነወ

Reply
Sisay Awoke September 29, 2025 - 9:54 am

ለምን ከሰሜን ኮሪያ ጋ ተጣልታችሁ ወደኛ ኒኩለር ተኩሳ አንዴ እንድትጨርሰን ብታደርጉ ውለታ መላሽ ነን

Reply
Eto-kranyo Eto-Kranyo September 29, 2025 - 9:54 am

ብልፅግና ይችላል¡¡¡😁

Reply

Leave a Comment