banner

“ትውልዱን በትምህርት እና በቴክኖሎጂ ማብቃት የህልውና ጉዳይ ነው” አቶ ሽመልስ አብዲሳ

#FastMereja I የኦሮሞ ጥናት ማህበር በተለያየ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተጻፉ አራት መጻህፍት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ተመርቀዋል።

አቶ ሽመልስ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ በትምህርት እና በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ የማፍራት ሥራ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶታል። በተለይም ትውልዱን በትምህርት እና በቴክኖሎጂ ማብቃቱ የህልውና ጉዳይ መሆኑን አንስተው፣ በዚህ ረገድ ባለፉት ዓመታት ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ጥናት ማህበርም እውቀትን ማዕከል በማድረግ እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች የሚበረታቱ መሆኑን ገልጸው የክልሉ መንግስትም ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የኦሮሞ ጥናት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ በበኩላቸው ማህበሩ የኦሮሞ ባህል፣ ታሪክ እና የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ጥናቶችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በተጨማሪም አጠቃላይ የኦሮሞ ህዝብ አኗኗር እና ነባር እሴቶችን ማጥናትና ለአሁኑ ትውልድ ማሳወቅ እንዲሁም የህዝቡን የኢኮኖሚ ሁኔታ በመቃኘት የመተንተን ስራ እያከናወነ መሆኑን አመልክተዋል።

ዛሬ ለምረቃ የበቁት አራቱ መጻህፍትም ትውልዱ እውቀትና እውነት ላይ ተመስርቶ እንዲወያይ፣ እንዲነጋገርና እንዲግባባ የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።

ከመጻህፍት ምረቃው ጎን ለጎን ለአፋን ኦሮሞ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ቀደምት ምሁራን እውቅና የተሰጠ ሲሆን በዚህም የሼክ በክሪ ሳጳሎ እና የሀይሌ ፊዳ ቤተሰቦች እውቅናውን ተቀብለዋል።

የክልሉ መንግስት እውቅና ለተሰጣቸው ለሁለቱ ምሁራን ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው የአምስት ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

#ልዩ_ልዩ





4 comments

Netsanet Tafese September 28, 2025 - 5:06 pm

ኦኦ😔

Reply
Eyesus Kirstos Bezanew September 28, 2025 - 5:06 pm

🙄

Reply
Said Muhammed Yesuf September 28, 2025 - 5:07 pm

ewnt nw

Reply
Ky Seife September 28, 2025 - 5:07 pm

ወግ ወጉን ይዘሀል ጦርነት ማግዱን እንጂ

Reply

Leave a Comment