banner

አቶ ዮናስ አለማየሁ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ “መሶብ” አገልግሎት ዋና ስራ-አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

​#FastMereja | የአዲስ መሶብ ዲጂታል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዮናስ አለማየሁ፣ ከየካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የ“መሶብ” አገልግሎት ዋና ስራ-አስፈፃሚ ሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) መሾማቸው ታወቀ።

​አቶ ዮናስ አለማየሁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት (አዲስ መሶብ) በደንብ ቁጥር 193/2017 ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ፣ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ ቆይተዋል።

​የአዲስ መሶብ ስትራቴጂክ እና ጠቅላላ ካውንስል እንዲሁም ሰራተኞች፣ አቶ ዮናስ ተቋሙን ከማደራጀት ጀምሮ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

#ልዩ_ልዩ

Leave a Comment