#FastMereja I በማህበራዊ ሚዲያ በጎ ተፅዕኖ ለሚያሳድሩ፣ ለውጥ ለሚያመጡ ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና የሚሰጠው “የቅን ልቦች” ፕሮግራም፤ የየካቲት ወር 2018 ዓ.ም የውድድር ውጤቱን ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት አዶናይ (Adonay) እና አቲስ ነማ ቻሪቲ (Atis Nema Charity) የወሩ አሸናፊ በመሆን እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ለ100 ግራም ንጹህ ወርቅ የሚደረገው ፉክክር
የዘንድሮው የ”የቅን ልቦች” ውድድር ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን የሳበው ለዓመቱ ማጠቃለያ በተዘጋጀው ታላቅ ሽልማት ነው። የፕሮግራሙ አዘጋጆች እንዳስታወቁት፣ በዓመቱ ማጠቃለያ ላይ በየወሩ ከሚካሄዱት ውድድሮች ብዙ ወሮችን በአሸናፊነት ማጠናቀቅ የቻለ ግለሰብ ወይም ተቋም የ100 ግራም ንጹህ ወርቅ ባለድል ይሆናል።
እስከ የካቲት ድረስ ያለዉ የአሸናፊዎች ዝርዝር፡-
ውድድሩ ከተጀመረበት ከነሐሴ ወር ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየወሩ ድል የቀናቸው ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሚከተሉት ናቸው፦
📍ነሐሴ፦ Brook News
📍መስከረም፦ Adonay
📍ጥቅምት፦ ዶክተር አብይ እና ማስተር አብነት
📍ህዳር፦ ጉርሻ ፔጅ
📍ታህሳስ፦ ሜላት ንጉሴ እና Adonay
📍ጥር፦ ጆን ዳንኤል
📍የካቲት፦ አዶናይ እና አቲስ ነማ ቻሪቲ
የአሸናፊነት ጉዞው ወዴት ያመራል?
ፕሮግራሙ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰሩ በጎ ስራዎችን በማበረታታት እና ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ተግባራትን በማጉላት ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
#ልዩ_ልዩ
