0
#FastMereja I ከ36 ዓመታት በላይ በነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አገልግሎት ለ9,000 በላይ ታካሚዎች አገልግሎት የሰጠው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ሕጻናት መርጃ ኅዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም “ደጋግ እጆች ለልጆች” በሚል መሪ ቃል የሩጫ መርሐ ግብር ሊያካሂድ እንደሆነ አስታወቀ።
4,000 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ ሲሆን መርሐ ግብሩ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ይጀምራል፣ መድረሻውም በሜክሲኮ ለገሀር በብሔራዊ አድርጎ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይጠናቀቃል።
ከዚህ መርሐ ግብር ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ ቀጣይ የሩጫ ውድድር ደግሞ በሀዋሳና በተለያዩ ክልል ከተሞች እንደሚካሄድ ተነግሯል።
ተቋሙ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ለሚመጡ ታካሚዎች ሁሉ ከከፍያ ነጻ የልብ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሆነም ተጠቀሰ።



