#FastMereja I በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ7ኛ ጊዜ የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን 2025 ትኩረት ያደረገና “ደህንነቱን የጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ ህፃናት እና ህፃናት በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
በላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል የተከበረው የዘንድሮው የህሙማን ደህንነት ቀን የሚከበርበት አላማ በምርመራ ጊዜ የሚከሰቱ ስህተቶችን እና የህሙማን ደህንነት ላይ ያላቸውን አሉታዊ ተጽዕኖ እንዲሁም ጊዜውን የጠበቀ እና ትክክለኛ የምርመራ አገልግሎት ለህሙማን ደህንነት ያለው በጎ ተጽዕኖ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን ተነግሯል።
የላንድማር ሆስፒታል ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ከበደ ወሊ የህሙማን ደህንነት ቀን የሚከበርበት ዓላማ በህሙማን ደህንነት ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል።
ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሕሙማንና የጤና ሙያ ማህበራት፣ ፖሊሲ አውጪዎችና የልማት አጋሮች ተቀናጅተው የህሙማንን ደህንነት ለመጠበቅ እንደሚቻል ተናግረዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፣ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ፣የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ፣የተለያዩ ዲፕሎማቶችና የኤምባሲ ተወካዮች፣ የአጋር ድርጅቶችና አጋር አካላት ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#ኹነት




