banner

ረዳት ሜዲካል ፕላዛ ከ“ንጋት” የጡት ካንሰር ድጋፍ ማህበር ጋር በመተባበር የግንዛቤ ውይይት አደረገ!

#FastMereja I በጡት ካንሰር ላይ ይህ የግንዛቤ ውይይት የተረፉ ሴቶች ድምጽ እንዲጠነክር፣ ቀደም ብሎ መከላከል እንዲበረታ እና በሕክምና ላይ የበለጠ ግንዛቤ እንዲፈጠር ያስቻለ መድረክ እንደሆነ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የጡት ቀዶ ጥገና ሐኪሞች፣ ኦንኮሎጂስቶች እና የ“ንጋት” ድጋፍ ቡድን አባላት እይታዎቻቸውን አካፍለዋል።

በአለም ዙሪያ በመስከረም እና ጥቅምት ወራት የሚከበረው “የጡት ካንሰር ግንዛቤ መፍጠር ወር” በሚል የሚከበረው የግንዛቤ መፍጠር ወር በረዳት ሜዲካል ፕላዛ ሴቶች ለአንድ ወር በነፃ የቅድመ ጡት ካንሰር ምርመራ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

እንዲሁም በዚህ ወር ውስጥ የማሞግራፊ እና የአልትራሳውንድ ምርመራዎች በ25% ቅናሽ እንደሚሰጥ የረዳት ሜዲካል ፕላዛ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ብሩክ ፍቃዱ ተናግሯል።

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በካንሰር የተያዙ ሰዎች በህይወት የመቆየት እድል 50 ከመቶ በታች እንደሆነ ተነግሯል። ለዚህም ምክንያቱ ሰዎች በካንሰር ተይዘው ህመሙ ተባብሶ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ሃኪም ቤት ስለሚመጡ ነው ተብሏል።





Leave a Comment