banner

“ሶስት ልጆቼን በ1 ጡት ነው ያሳደኩት” አትሌት ጌጤ ከባድ ችግር ውስጥ ነች!

#FastMereja I አትሌት ኮማንደር ጌጤነሽ ኡርጌ ትባላለች በአትሌቶች መፍለቂያ አርሲ ነው የተወለደችው፣ የመጀመሪያ ውድድሯን በ1982 በካናዳ ወጣቶች ውድድር ነው የተካፈለችው፣ ከዛም የባርሴሎና ኦሎምፒክ ጨምሮ በእንግሊዝ፣ ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ኖርዌይ፣ ቤልጂየም፣ ጣሊያን፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን፣ እና በአፍሪካ በተለያዩ ሀገራት እስከ 2000 ዓ.ም ተወዳድራ የወርቅ፣ ብር እና ነሃስ ሜዳልያ አሸናፊ በመሆን ሀገሯን ከእነ ደራርቱ ቱሉ እና ጌጤ ዋሚ ጋር አስጠርታለች።

በሜሪ ዲዳ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው ካሜቲ ፖድካስት ላይ ቀርባ እንደተናገረችው ህይወቴ መልኩን የቀየረው ሁሉንም ነገር ያጣውት በካንሰር ከተያዝኩ በኋላ ነው ብላለች።

አምስት ልጆች የነበሯት አትሌት ጌጤነሽ አንዷ ልጇ በጭንቅላት ካንሰር ከሁለት አመት በፊት ህይወቷ አልፏል፣ አሁን 4 ልጆች ያሏት ሲሆን 3 ልጆች የተወለዱት በካንሰር ምክንያት አንዱ ጡቷ ከተቆረጠ በኋላ እንደሆነ ተናግራለች። በአንድ ጡት ሶስት ልጆቿን እንዳሳደገች ገልጻለች።

ያሏትን በለቶች ንብረት ሁሉንም ሸጣ አሁን ከአዲስ አበባ በመውጣት ዱከም አከባቢ ገጠር ውስጥ የሰው ቤት ውስጥ ኑሮዋን አድርጋ ትገኛለች።

የአትሌት ጌጤ ስጋት ህይወቴ ቢያልፍ ልጆቼ ሜዳ ላይ ጥያቸው ነው የምሄደው ሁሌም የሚያሳስበኝ ይህ ነው ብላለች። በችግር ምክንያት ባለፈው አመት ትምህርት ቤት ያልሄዱት ልጆቿ ምንም መተዳደሪያ ስለሌለኝ ህይወቴ በጣም የከፋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል ብላለች።





Leave a Comment