0
#FastMereja I ኤስቴቲክ ኢንተርናሽናል ክሊኒክ በስነውበት ሕክምና ላይ በበርካታ ሀገራት የሚሰራ ዝነኛ ክሊኒክ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ካሉት 8 ቅርንጫፎች በተጨማሪ ዘጠነኛውን ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ መክፈቱ አስታውቋል።
አቮራ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር በስነውበት ሕክምና በተለይም በፕላስቲክ ሰርጀሪ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ከሆኑት የሕክምና ተቋማት አንዱ የሆነውን ኤስቴቲክ ኢንተርናሽናል ክሊኒክ በኢትዮጵያ በፍራንቻይዝ መክፈቱ ተገልጿል።
በዘርፉ 26 አመታትን ያስቆጠረው ክሊኒኩ ከሚሰጣቸው የፕላስቲክ ሰርጀሪ መካከል የብልት፣ የመቀመጫ፣ የደረት፣ የጸጉር፣ የፊት፣ የደረት ተጠቃሽ ናቸው።
አቮራ ቢዝነስ ግሩፕ በወጪ ንግድ ላይ የተሰማራ ሀገር በቀል ኩባንያ ሲሆን ድርጅቱ በዘርፉ ለሀገር እያበረከተ ከሚገኘው ቀጥተኛ አስተዋጽዖ በተጓዳኝ ከተመረጡ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር ችግር ፈቺ የሆኑ አገልግሎቶችን/ ግኝቶችን ወደ ሀገር ውስጥ በማምጣት የተሻለ ማኅበረሰባዊ ተጠቃሚነት ይፈጠር ዘንድ የበኩሉን ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ ባለራዕይ ተቋም እንደሆነ ተነግሯል።
#ቢዝነስ





1 comment
በቃ ሊያትሙት ነው👏👏