banner

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሀገር በቀል የውበትና የጤና ፌስቲቫል ተዘጋጀ

#FastMereja I በራዲያንስ ፌስት አዘጋጅነት የተዘጋጀዉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የአገር በቀል የዉበትና የጤና እንክብካቤ ፌስቲቫል በዛሬዉ እለት ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም በሀያት ፌጀንሲ ሆቴል በታላቅ ድምቀት ተከፍቷል።

ራዲያንስ ፌስት የውጪ ውበትን ከማጉላት ባለፈ ከኢትዮጵያ ሰፊ የእፅዋት ቅርስን ከዘመናዊ አቀራረቦች ጋር በማቀናጀት ሁለንተናዊ የጤና አጠባበቅን እንደ አኗኗር ዘይቤ አድርጎ መከተልን እንደሚያበረታታ ነዉ የተገለፀዉ፡፡

የኢትዮጵያን የውበት እና የጤና ዘርፍ ታሪክ ከፍ የሚያደርግ ራዲያንስ ፌስት 2025 የተሰኘ የግል ጤና አጠባበቅን ወደ ፊት የሚያራምድ፣ ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ የኢትዮጵያ ጤና መጠበቂያ መንገዶችን የሚያጎላ የመጀመሪያው ግዙፍ ፈስቲቫል እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህ ፌስቲቫል ላይ የቆዳ እንክብካቤ፣ የዕፅዋት መድኃኒቶች፣ የአካል ብቃት፡ የአመጋገብ እና የውበት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የአገር ውስጥ አምራቾችን የሚያቀራርብ ሲሆን፣ በተፈጥሯዊና ኦርጋኒክ ውህዶችን እንዲሁም በሳይንስ የተደገፉ ዘመናዊ ምርቶችን፣ ለጥራት፣ ለደህንነት እና ለአገር ውስጥ ምርት እድገት ትኩረት የሚሰጡ ሲሆን የተለያዩ የአገር ውስጥ ምርቶችም በአንድ መድረክ እንዲቀርቡ እድል ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል።

ራዲያንስ ፌስት ጤና የግል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የስራ እድል የሚፈጥር እንዲሁም ለኢኮኖሚ እድገት አንድ ግብዓት መሆን እንደሚችል ነዉ የተገለፀዉ።
ራዲያንስ ፌስት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ጥቅምት 21-22 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁሉም ክፍት ይሆናል፡፡

#ኹነት





Leave a Comment