#FastMereja I “ያለፈ ታሪካችን የወደፊት ህይወታችንን አይወስነውም” ይልቁንም ያበረታናል በሚል መሪ ቃል በዛሬዉ እለት ጥቅምት 29/2018ዓ.ም የመጀመሪያዉ የኢትዮጵያ ኬር ሊቨርስ ቀን ተከብሯል።
ይህ የመጀመሪያዉ ኬር ሊቨርስ ቀን ከአማራጭ ህፃናት እንክብካቤ እና ድጋፍ አድገው 18 አመት ከሞላቸዉ በኋላ የወጡ ወጣቶች ያለፉትን የማይታመን ጥንካሬ፣ ብርታት እና ያልተገደበ አቅም እንዲሁም የህፃናቱን እና ወጣቱን ነፃነት እና የራስን እጣ ፈንታ የመወሰን አቅም የሚያረጋግጥ ኃይል ያለው ትልቅ መድረክ እንዲሁም ፓናል ዉይይት ተካሂዷል።
ዛሬ በተካሄደዉ ፓናል ዉይይት ላይ የስራና ክህሎት ማኅበር ኬር ሊቨርስ በጎ አድራጎት ማኅበርና የቀድሞ ኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር ወጣቶች ማህበር ኢትዮጵያ ልምዳቸውን ያለፉባቸውን ፈተናዎች፣ ያገኙዋቸውን መልካም ዕድሎች፣ እና ወሳኝ የሆኑትን ትምህርት የሚሆኑ ነጥቦች እንዲሁም በማኅበር ለመደራጀት ሂደት ላይ ላሉ ከተለያዩ ተቋማት አድገው ለወጡ ወጣቶች ለወደፊት ምን መሰራት እንዳለበት ነጥቦች ተነስተዉ ምላሽ ተሰቶባቸዋል።
በዚህ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኬር ሊቨርስ ቀን ታላቅ ተስፋን ያቀጣጥላል ፣ ጥልቅ ግንኙነቶችን ያነሳሳል እንዲሁም ሁሉም በአማራጭ ህፃናት እንክብካቤ እና ድጋፍ ያለፈው ሰው ስኬታማ የሚሆንበትን የወደፊት ጊዜ መንገድ ይከፍታልም ተብሏል።
ከብሄራዊ አማራጭ ህፃናት እንክብካቤ እና ድጋፍ አድገው የወጡ ወጣቶች ያሳለፉት አለመረጋጋት ጥልቅ የአእምሮ ጤና ጉዳቶችን (ከድብርት እስከ post-traumatic stress disorder PTSD) ይዞ እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል ስለዚህ ያለፈውን ቁስላቸውን ለመፈወስ ልዩ እና ዘላቂ የአእምሮ ጤና አገልግሎት መሰጠት እንዳለበትም ተገልጿል።
“ብሔራዊ አማራጭ የህፃናት ክብካቤ አድገው የወጡ ማህበራት ህብረት ጥምረት”በአማራጭ የህፃናት እንክብካቤ ያደጉ ወጣቶች ከእንክብካቤ ስርዓቱ ሲወጡ የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች ለመቅረፍ ” የበኩሉን እየተወጣ የሚገኝ ማህበር ነው፡፡




