banner

ተመራጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ሁለተኛ አመት የምስረታ በአል አከበረ!

#FastMereja I ተመራው የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ሁለተኛ አመት የምስረታ በአሉን በዛሬዉ እለት ህዳር 6/2018ዓ.ም በማዶ ሆቴል አክብሯል።

ተመራጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ህዳር 2/2016ዓ.ም በአቶ ዘዉዱ ሰብስቤ ተመስርቶ ወደ ሁለት መቶ ስልሳ አራት አባላትን ይዞ በስድስት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር ካፒታል ነው ስራ የጀመረው።

በሁለት ዓመት ቆይታ ውስጥ ከአራት ሺህ በላይ አባላት በሶስት መቶ ሰላሳ ሚሊየን ብር አካባቢ የሚጠጋ ሀብት መፍጠር መቻሉን እና ለሁለት መቶ ሰላሳ አባላቶች ወደ ሁለት መቶ ሰማንያ ሚሊየን ብር ብድር መስጠት የቻለ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።

ሰባት በሚሆኑ ልባም ጓደኛሞች ሰብስቦ የተነሳዉ ይህ የቁጠባና ብድር ማህበር ከተነሳበት አላማ አንፃር ከተማ ውስጥ ካሉት የገንዘብ ቁጠባ ብድር የተሻለ አሰራር በአባላት ቁጥር፣ በካፒታል መጠን፣ በጠቅላላ ሀብት እንዲሁም ከወለድ አንፃር ከሌሎቹ የብድርና ቁጠባ ማህበራት የተሻለ አሰራር ይዞ መምጣቱን የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዘዉዱ ሰብስቤ ገልፀዋል።

ይህ የህብረት ስራ ማህበር በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የእባላት ቁጥሩን ወደ ሃምሳ አራት ሺህ ለማሳደግ እንዲሁም ሃያ ሰባት ቅርንጫፍ ለማድረስ የሰራተኛ ቁጥርን ለመጨመር እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ህብረት ስራ ማህበሩ ሰራተኞችን በእውቀት በክህሎት የዳበሩ ለማገልገል የተዘጋጁ ብቃት ያለው ሰራተኛ ከመቅጠር አንፃር እና ተመራጭ አንዱ ኳሊቲ ሰራተኞቹ በገንዘብ (ደሞዝ) መደገፍ እንደሆነም ተገልጿል።

በሁለተኛ አመት የምስረታ በአሉ ላይ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶት የማህበሩ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸዉ አካላት በተገኙበት በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተከብሯል።





Leave a Comment