0
#FastMereja I የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በተመለከተ ችግር የነበረበት በመሆኑ ወጥ አሰራር መከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎች ዶክተር ወይንም የክብር ዶክተር በሚል መጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል።
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት ሀገራዊ እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው በመመሪያ መመላከቱን ያነሱት ክቡር ሚኒስትሩ፤ በሙያው የተለየ ስራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል ጠቅሰው ይሁን እንጂ የተሠጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አብራርተዋል።

10 comments
#የሱም መቀየር አለበት!!!
አረ ከሰማን ቆየ እኮ ፋስቶች ሌላ አዲስ ነገር ካለ ዘግቡ እንጂ🤭
ጠ ሚው አብይንም ነው
ጭር ሲል አልወድም የሆንክ ሰውዬ 🙄🙄
እና መጠሪያ ካልሆናቸው ወረቀቱማ ሳይማሩበት ምን ጥቅም
ይህች ጠጋ ጠጋ የመሪያችንን የክብር ስም ለመንኳት ነው አታሳ🤭
He thinks that he he thinks more than we thinks that all of us are thinks in the box of that thoutht😁🙄
ይሄ ነበር የቀረህ
እውቀት ከገንዘብ ይበልጣል ብዬ እንደተከራከርኩ ትዝ ሲለኝ
የጠቅላዩንም መጥራት አይቻልም ማለት ነው ?🙄🤔