banner

ብረሽድ ባይ ቤቲ ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም ተማሪዎቹን አስመረቀ

#FastMereja I ብረሽድ ባይ ቤቲ ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም ያስተማራቸውን ተማሪዎች ለ7ኛ ዙር ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም በወዳጅነት ፓርክ አስመርቋል።

በሜካፕ፣ በአይላሽ፣ በጥፍር እና በሌሎች ከ13 አይነት በላይ የተለያዩ የሜካፕ ስልጠናቸውን ተምረው ያጠናቀቁ 350 ተማሪዎች ተመርቋል።

ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ የራሳቸውን ስራ ለመጀመር ከፈለጉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቤተልሄም እስክንድር የተቋሙ መስራች እና ባለቤት ገልጸውልናል በተጨማሪው በዱቤ መማር የሚችሉበትን መንገድ እንዳለ ተናግሯል።

በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ በተማሪዎች የተሰሩ ሜካፕ ውድድር ቀርቦ አሸናፊ ተማሪዎች ተሸልማል።

ተቋሙ የራሱን BE Cosmetics የተሰኘ የሜካፕ ምርት ይፋ ያደረገ ሲሆን ከ20 በላይ የተለያዩ የሜካፕ ምርቶች ይኖሩታል ተብሏል።

በአዲስ አበባ 4 ቅርጫፍ ያለው BBMI በድሬዳዋ አዲስ ቅርጫፍ በመክፈት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።





Leave a Comment