0
#FastMereja I የስታንዳርድ ኢንሹራንስ አ.ማ. እና የአዋጭ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥ/ማህበር ስልታዊ የአጋርነት የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ሕዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተፈራረሙ።
ይሀ ስምምነት በሁለቱም ተቋማት አባላትና ባለድርሻ አካላት መካከል የሚሰጡትን የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ አገልግሎቶች ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ወቅታዊ በሆነ መልኩ ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
ሁለቱን የፋይናንስ ተቋማት በአንድ ላይ በማምጣት የማይክሮ ፋይናንስ እና የመድን ሥራዎቻቸውን በጋራ ጥቅም እና መግባባት መርሆዎች ላይ ተመሥርቶ ለማጎልበት ታስቦ የተፈጠረ ጥምረት መሆኑ ተነግሯል።
በዚህ አጋርነት ስታንዳርድ ኢንሹራንስ በአዋጭ የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት ተቀማጭ ገንዘብ ያስቀምጣል። አዋጭ ደግሞ የኢንሹራንስ ክፍያዎችን በመሰብሰብ ለስታንዳርድ ኢንሹራንስ በፍጥነት ያስተላልፋል እንዲሁም የማስተዋወቂያና የሽያጭ ሥራዎችን ለመደገፍ በቢሮዎቹ ውስጥ ነፃ የሥራ ቦታ ያቀርባል።




