0
#FastMereja I የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማኀበር ምስረታን አስመልክቶ የማህበሩ አባላት ዛሬ ሕዳር 19/2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥቷል።
የማህበሩ ምስረታ ዋና አላማ ይዘት ፈጣሪዎች በቀረጻ ወቅት ከሚደርስባቸው ጫና በጋራ ሆኖ መከላከል እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከማህበረሰቡ ባህል እና ወግ ውጪ የሚሰሩ ሰዎች ለመከላከል እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም ያለ አግባብ የሚዘጉ አካውንቶችን ለማስከፈት እና አሉታዊ መልዕክት ያላቸውን ይዘት የሚሰሩ አካውንቶችን ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል።
ስምንት ወራት የፈጀው የማህበሩ ምስረታ በ19 አባላት እንደተመሰረተ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማኀበር በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ህዳር 12/2018 ዓ.ም ተመዝግቧል።
የማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ ከ5ሺህ በላይ ተከታይ እና ከ18 አመት በላይ ከሆነ አባል መሆን ይችላል ተብሏል።





10 comments
ሞጣስ💪
ግብር ለመክፈል😀
የማህበሩ አበል እንሆነለን።
Where is adonay?
አዶናይ ያሌለበት ፉርሽ የሆነ ማህበር ነው
ክፍያ መጀመር አለበት።
#ፍቅሩ_አብጤ
where is adonay
ዩቲ ግን በደናዋ ነዉ
Adonay የት አለ። 🤔