#FastMereja I ህዳሴ ገና 2018 ኤክስፖ ከታህሳስ 4 እስከ ታህሳስ 28/2018ዓ.ም ድረስ በመስቀል አደባባይ ኤግዚቢሽን ማዕከል በድምቀት ይካሄዳል።
በዳሶማ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተ/የግ/ማህበር አዘጋጅነት የተዘጋጀዉ ይህ ኤክስፖ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ይጎበኙታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዚህ ኤክስፖ ከ100 በላይ የሙዚቃ ሰዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነዉ የተገለፀዉ።
በዘንድሮ ኤክስፖ ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት፣ የሪል ስቴት አልሚዎች፣ የተሽከርካሪ መኪና አስመጪዎች፣ የሸማች ማህበራት የሸቀጣ ሸቀጥ እና የእለት ፍጆታ አቅራቢዎች፡ የአዋቂ እና የህፃናት አልባሳት እንዲሁም የቤት ውስጥ እቃዎችና የፈርኒቸር ውጤቶች የሚያቀርቡ ተቋማት ይገኙበታል።
በኤክስፖዉ ላይ የተጋነነውን የዋጋ ንረት ለማስቀረት ሽማቹ ምርቱን ቀጥታ ከአምራች እና አስመጪዎች ላይ የሚገበያይበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሲሆን የህፃናት ጌም ዞኖች እንዲሁም ጣፍጭ ምግቦችና መጠጦች በበቂ ሁኔታ እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
በኤክስፖ ላይ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ለበርካታ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ነፃ ቦታ በመፍቀድ ማህበራቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ የበዓሉም ዕለት እጅ ያጠራቸውን ወገኖች በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደስተው እንዲውሉ ዳሶማ ትሬዲንግ ድጋፍ ያደርጋል።
በተከታታይ 25 ቀናት በሚደረገው ኤክስፖ ላይ በየቀኑ የተለያዩ አጓጊ ሽልማቶች የሚኖሩ ሲሆን ታህሳስ 28 በሚኖረው የመዝጊያ ስነስርዓት ላይ የመኪና ሽልማት እንደሚበረከት ተገልጿል።
#ቢዝነስ መረጃ




