banner

ሹም ሽረት ፊልም ለህዝብ እይታ ሊቀርብ ነው።

#FastMereja I በዩሊያን ፊልም ፕሮዳክሽንና ከክብሪት ፒክቸርስ ጋር በጥምረት የተሰራው “ሹም ሽረት” ፊልም ከነገ ጀምሮ በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት እንደሚጀምር ዛሬ በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

ሹም ሽርት ፊልም በደራሲና ፕሮዲዩሰር ዩሊያን ተ/ማርያም ተደርሶ የቀረበ ሲሆን ፊልሙ 2.5 ሚሊየን ብር እንደወጣበትና አንድ አመት እንደፈጀ ተገልጿል።

አድማሱ ከበደ ፣ ፍቅርተ ደሳለኝ ፣ ማስተዋል ወንደሰን ፣ ዩልያን ተክለማርያም ፣ ትዕግስት ከበደ ፣ አብይ ዲንሳ እና ሌሎች ወጣት ተዋንያን በፊልሙ ላይ ተሳትፈውበታል ። ዩሊያን ተ/ማርያም ዳይሬክት አድርጎታል።

ዩሊያን ፊልም ፕሮዳክሽን የተለያየ የዶክመንተሪ ፣ የሚዲያ እና የፊልም ስራዎች በመስራት ይታወቃል።





Leave a Comment