banner

“ዛሬ ይማሩ፣ ገቢዎ ሲጀምር ይክፈሉ!” ተባለ።

#FastMereja I ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ እና ጆርዳን ቢዩቲ አካዳሚ የሴቶችን ህይወት የሚቀይር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ስምምነት የሁለቱንም ተቋማት የላቀ ማኅበራዊ ኃላፊነት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ የበርካታ ሴቶችን ሕይወት በመለወጥ ረገድ አብዮታዊ እርምጃ ለመውሰድ ያለመ ልዩ ፕሮጀክት መሆኑ ተነግሯል።

የድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ የፋይናንስ ዕድል ሲፈጥር፣ የጆርዳን ቢዩቲ አካዳሚ የሙያ ስልጠናዎችን ይሰጣል።

ይህ ትብብር “ዛሬ ይማሩ፣ ገቢዎ ሲጀምር ይክፈሉ!” በሚለው መርህ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይህም በርካታ ሴቶች የፋይናንስ እገዳ ሳይኖርባቸው የሙያ ህልማቸውን እንዲያሳኩ ያስችላቸዋል ተብሏል።

JBA ሴቶች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባለው ሰርተፍኬት የውበት ባለሙያ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ዘመናዊና የተሟሉ የፀጉር፣ ሜካፕ፣ የጥፍር ጥበብ እና ሌሎች የውበት ሙያ ስልጠናዎችን ይሰጣል። ይህም ሴቶች በፍጥነት ገቢ የሚያስገኙ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ በማድረግ ለሥራ ፈጠራና ለራስ ምቹ የሥራ ዕድል ይፈጥራል፤ ሥራ አጥነትን በመቀነስና የማህበረሰቡን የምርትና አገልግሎት አቅም በማሳደግ በኩል የበኩሉን ይወጣል።





Leave a Comment