0
#FastMereja I በኮንስትራክሽን ስራ ከተሰማራ 17 አመት ያስቆጠረው አሁን በሪል ስቴት ስራ ሶስት አመት የሆነው አልቲማ ሪል ስቴት በግንባታ ዘርፍ ረጅም አመታትን ያስቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች የመሰረቱት “ህልምዎን ይኑሩ” በሚል መሪ ቃል ቤቶችን እየገነባ ይገኛል።
በሶስት አመታት ሁለት ግንባታዎችን አጠናቆ ያስረከበ ሲሆን አንድ ግንባታው ደግሞ ለመጠናቀቅ 80% በላይ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
አልቲማ ሪል ስቴት ባለ 2ዐ ወለል ግንባታ በመስቀል ፍላወር ቱሊፕ ኦሎምፒያ ጎን ያስጀመረ ሲሆን በዛሬው እለትም በማስታወቂያ፣ ፊልም እና ቴአትር ላይ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለውን አርቲስት ነፃነት ወርቅነህን የድርጅቱ የአልቲማ ሪል ስቴት የብራንድ አምባሳደር በማድረግ ስምምነት ፈጽሟል።
በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ፈለጊውን የኑሮ ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሆን ከ2.7 ሚሊየን ብር ጀምሮ ቤቶችን በማቅረብ አልቲማ ሪል ስቴት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
#ቢዝነስ መረጃ





3 comments
እንዴ ምነው ሾቀሳ🙄
ሰውነቱ ቀንሷል🥺
Netsanet tamowal