banner

ከጥር 23 ጀምሮ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀምና ማምረት በህግ ያስቀጣል

#FastMereja I ​የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች ላይ የተጣለው እገዳ ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንደሚሆንና እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።

​ዋና ዋና ነጥቦች፦
📌 ​የእገዳው ገደብ፦ የ6 ወራት የሽግግር ጊዜው ጥር 23 ያበቃል። ከዚህ ቀን በኋላ ስስ ፕላስቲኮችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና መጠቀም በህግ ያስጠይቃል።

📌 ​አማራጭ አቅርቦቶች፦ የወረቀትና ሌሎች ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ከረጢቶችን ለሚያመርቱ አካላት የማሽነሪ ከቀረጥ ነፃ መብትና የብድር አቅርቦት እንዲመቻች እየተሰራ ነው።

📌 ​የክትትል ስራ፦ ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በገበያ ውስጥ የሚታዩ ህገወጥ የፕላስቲክ ስርጭቶችን ለመቆጣጠር ዝግጅቱን አጠናቋል።

🚨 ​ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም ነጋዴም ሆነ አምራች እስከ ጥር 23 ድረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ወደ አማራጭ ምርቶች እንዲሸጋገር ጥሪ ቀርቧል።

3 comments

Geremew Gedefaw Alemu December 22, 2025 - 10:15 am

የዘንድሮ ቅጣት ሆድ ይፍጀዉ ደሃ ዳቦ፣ ሙዝ፣ አትክልት፣ የቤት አስቤዛ በምን ቋጥሮ ወደ ቤቱ ይግባ

Reply
Dagne Man Liverpool December 22, 2025 - 10:17 am

ይሄን ዳቦ በልቶ ያልጠገበ ህዝብ ግራ አታጋቡት ።

Reply
Na'ol Zelalem Bacha December 22, 2025 - 10:17 am

ለመከልከል ብቻ ሳይሆን መፍትሄም ማምጣት ነው

Reply

Leave a Comment