banner

ቴምር ፕሮፐርቲስ 12 ሚሊዮን ብር ሽልማት አዘጋጀ።

#FastMereja I “የቴምር ስጦታ ኤከስፖ” ከታህሳስ 25 ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ ዛሬ በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

በዚህ ኤክስፖ ቴምር በሪል ስቴት ዘርፉ ባለፉት 10 አመታት ያከናወናቸው አበይት ስኬታማ ስራዎች ይቀርባሉ፤ በግንባታ ላይ ስለሚገኙ ፕሮጀክቶችም ማብራሪያ ይሰጣል ተብሏል።

በአያት ፈረስ ቤት እና በሳርቤት ሰከን ሳይቶች ቴምር ግንባታ ሳይጀምር አምነው ሙሉ ከፍያ የፈጸሙ ደንበኞች ሁለት ቢዋይዲ ኢቱ መኪኖች እንዲሁም ለአራት ሰዎች በድምሩ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የፊኒሺንግ ስራዎች። በአጠቃላይ 12 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ትልልቅ ስጦታዎች ለታማኝ ደንበኞች በእጣ ይሰጣሉ።

ቴምር ፕሮፐርቲስ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም “ኑ የህልምዎ ማረፊያ ቤትዎን ለመገንባት አብረን እንምከር” ብሏል።

በሁለት ባለ ራዕዮች ምስረታውን በ2008 ዓ.ም ያደረገው ቴምር ፕሮፐርቲስ ከአስር አመታት በላይ በሪል ስቴት ልማት ላይ ልምድ ያለው ድርጅት ነው።

ቴምር በ10 አመት ውስጥ ከ10 በላይ ህንጻዎች ገንብቶ ያስረከበ ሲሆን አሁንም ከ28 በላይ ሳይቶችን እያንቀሳቀሰ ይገኛል።

#ኹነት





Leave a Comment