banner

15ኛው ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

#FastMereja I የአፍሪካን የፈጠራ ጥበብ ከዓለም አቀፍ የፋሽን ኢንዱስትሪ ጋር በማገናኘት ግንባር ቀደም የሆነው “ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ” (HAFW) 15ኛው ህግጅት ከጥር 5 እስከ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም (January 13-17, 2026) በአዲስ አበባ ሃያት ሪጀንሲ ሆቴል እንደሚያካሄድ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

​ባለፉት 15 ዓመታት መድረኩ ከ250 በላይ አህጉራዊ ብራንዶችን ያስተዋወቀ ሲሆን፣ ከ1,000 በላይ ሞዴሎችና ከ200 በላይ ዲዛይነሮች የሥራ ዕድልና ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ ድልድይ ሆኗል።

የዝግጅቱ መስራች ማህሌት ተክለማርያም በዓለም አቀፉ የፋሽን መረጃ ማዕከል “BOF 500″ (Class of 2025) ውስጥ ተካታ ዕውቅና ማግኘቷ ለዘንድሮው ዝግጅት ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል።

​የዘንድሮው ዝግጅት ላይ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ካሜሩን እና ሩሲያ የተውጣጡ አንጋፋና ጀማሪ ዲዛይነሮች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

በ”ጉዞ ቴክኖሎጂስ” አማካኝነት በቨርቹዋል ሪያሊቲ (VR) የታገዘ የፋሽን ትርዒት ለዕይታ ይቀርባል። የፋሽን ዘርፍ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ስላለው የ31 ቢሊዮን ዶላር ተፅዕኖ በባለሙያዎች የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ይደረጋል።

​ዝግጅቱ “ለነገው” (Lenegew) ከተሰኘውና አስቸጋሪ ሕይወት ያሳለፉ ሴቶችን ከሚደግፍ ፕሮጀክት ጋር በመሆን የልገሳና የምክር አገልግሎት መርሐግብር ይኖረዋል።

​በመዝጊያ ዕለቱ የሀገር ውስጥ የጥበብ ውጤቶች፣ የውበት መጠበቂያዎችና የቤት ውስጥ ዲኮሮች ለሽያጭ የሚቀርቡበት የገበያ መድረክ (Popup marketplace) ይዘጋጃል።

​ይህ ታላቅ መድረክ የአፍሪካን ፋሽን ትረካ ለመቀየር፣ ተሰጥኦዎችን ለማሳደግና አህጉራዊ ትስስርን ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።





Leave a Comment