#FastMereja I ትምህርትና ማህበራዊ ልማት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ግሎሪ የተቀናጀ ልማት ፋውንዴሽን በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ እጅግ ዘመናዊና ግዙፍ የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (Boarding Institute) መንደር ሊገነባ መሆኑን በዛሬው ዕለት በጌትፋም ሆቴል በሰጠው መግለጫ ይፋ አደረገ።
የፋውንዴሽኑ መስራች ወይዘሮ አስማሩ በሪሁን ከበደ እንደገለጹት፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በጎንደር ከተማ በ72 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፍ ይሆናል። ይህ ፕሮጀክት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትንና ግዙፍ ህንጻን የሚያካትት ሲሆን፣ ፋውንዴሽኑ በቀጣይ መሰል ተቋማትን በስምንት የሀገሪቱ ክልሎች ለማስፋፋት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁ ተገልጿል።
ለዚህ ግዙፍ ሀገራዊ ፋውንዴሽን ስራ ከፍተኛ ንቅናቄ ይፈጥራል ተብለው የታመነበት አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉን የድርጅቱ አምባሳደር አድርጎ ሰይሞታል።
የጎንደር ልዩ አዳሪ ኢንስቲትዩት ሲጠናቀቅ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ከ9-12ኛ ክፍል ያሉ ውጤታማ ተማሪዎችን በመቀበል፣ ሙሉ የመኝታና የምግብ አገልግሎት በነፃ በማቅረብ ለዩኒቨርሲቲ ብቁ ማድረግ።
የሙያ ስልጠና፡ ለወጣቶች ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ራሳቸውን እንዲችሉ ማገዝ።
የሴቶች ድጋፍ፡ ለሴቶችና ልጃገረዶች በሁሉም ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠት።
የማህበረሰብ ልማት፡ ለአካባቢው ማህበረሰብ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን መስጠት።
ግሎሪ የተቀናጀ ልማት ፋውንዴሽን በኢፌዴሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በምዝገባ ቁጥር 7356 ተመዝግቦ በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ የዘለቄታ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።
ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ (የባንክ አካውንቶች)
ለዚህ በጎ አላማ አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚከተሉትን የባንክ ሂሳቦች መጠቀም ይቻላል፡
1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አጎዛ ቅርንጫፍ): 1000656405302
2. አባይ ባንክ (ቅሊንጦ ቅርንጫፍ): 9281811942385026
3. ዳሽን ባንክ (ኡራኤል ቅርንጫፍ): 5815864198011





1 comment
እኔ ደሞ የ taxi ሰልፍ ላይ የታየ መስሎኝ 🤔🫣🫣