0
#FastMereja I የኢቢኤስ ቴሌቪዥን በፕሮግራም አቅራቢነትና በተዋናይነት ስመጥር የሆነው ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን በይፋ ገለጸ።
ቴሌቪዥን ጣቢያው ባወጣው የሀዘን መግለጫ፣ ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ሲተላለፍ የነበረውና የብዙዎችን ልብ የገዛው “የቤተሰብ ጨዋታ” ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የነበረው ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም መለየቱን በጥልቅ ሀዘን አስታውቋል። ባለሙያው በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት ብቻ ሳይሆን በፊልም ተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ዘርፎችም በተመልካቾች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበረ የጥበብ ሰው ነው።
ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት እንደነበር የገለጸው ጣቢያው፤ የኢቢኤስ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በባለሙያው ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ ባልደረቦቹና ለአድናቂዎቹ በሙሉ መፅናናትን ተመኝተዋል።

10 comments
RIP
Rip.
RIP
RIP
Rip😭😭😭
Rip😭😭😭
RIP
Rip
RIP😭😭
May your soul rest in eternal peace!!😭😭😭😭😭😭😭😭😭